Icona Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ

6.1.1 by ብራና አፕስ Birana Apps


Apr 28, 2021

Informazioni su Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ

La prima completa Bibbia etiopica ortodossa in Geez, amarico e inglese.

በይዘቱ ተሟልቶ በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የተዘጋጀ የመጀመሪያው ምሉዕ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ደንብ ጠብቆ የተዘጋጀ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዲሁም የቀኖና መጻሕፍት ብላ በ 1962 ዓ.ም ያሳተመችውን መጽሐፍ ቃል በቃል ለቅሞ መዝግቧል።

መጽሐፉ ለሃይማኖት አባቶች ለሰባክያነ ወንጌልና ለመምህራን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ በሚሰማሩበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው መያዝ ሳይኖርባቸው በቀላሉ እግዚአብሔርን ለማስተማር ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል :: ምዕመናንም የግዕዙንና የአማርኛውን ትርጉም ምሥጢሩ ሳይዛባ በስልካቸው እንዲጠቀሙ ይረዳል ::

የመጽሐፉ ልዩ ባሕርያት

• ሰማንያ አንድ (81) መጻሕፍትን ያካተተ ነው።

• ሙሉ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በግዕዝ ፣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ነው።

• የአማርኛው ትርጉም በጥንታዊው የአባቶቻችን አጻጻፍና አገላለጽ ሃይማኖታዊ ለዛውን ሳይለቅ የተጻፈ ነው።

• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸውን የብሉይና የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍትን ያካተተ ነው።

• ፊደሉና አጻጻፉ በግእዝና በአማርኛ መዛግብተ ቃላት መሠረት ታርሞ የተዘጋጀ ነው።

• የፊደሎችን መጠን በቀላሉ ማስተካከያ መንገድ አለው።

• በቀንና በጨልማ ለማንበብ የራሱ ማስተካከያ ተካቶበታል።

• ማስታወሻ መያዣ ፣ ማቅለሚያ ፣ ዕልባት ማድረጊያ ተካቶበታል።

• ማጣቀሻዎች በየቁጥሩ የተካተቱ ሲሆን በቀላሉ አንድ ጊዜ ብቻ ጠቅ በማድረግ ገጹን ሳይለቁ ማንበብ ያስችላል።

• በጣም ፈጣንና የፍለጋ ውጤቶችን በማቅለምና በቁጥር የሚያሳይ መፈለጊያ ተካቶበታል።

• የአማርኛ ፣ የግእዝና የእንግሊዝኛ ዕትሞችን ጎን ለጎን ፣ መስመር በመስመር ፣ ከላይና ከታች አድርገን ለማንበብ ያስችላል።

• የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በአኅጽሮት ወይም በሙሉ ስም ለመዘርዘር ማስተካከያ ተደርጎበታል።

• የፊደል መጠኑን በቀላሉ ማሳነስና ማሳደግ የሚያስችል ማስተካከያ ተካቶበታል።

• የመጽሐፍ ቅዱስ መስመሮችን እንድፍላጎትዎ ማስተካከል ይችላሉ።

• ከዚህ በፊት ያነበቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከዚህ በፊት የተነበቡ በሚለው ስር ያገኟቸዋል።

• የተለያዩ ቋንቋዎችን በመጠቀም የመጽሐፉን ይዘት መተርጎም ይችላሉ።

ከ 66 ቱ መጻሕፍት በተጨማሪ 19 የብሉይ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት እና 8 የአዲስ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍትን በግእዝና በአማርኛ አሟልቶ ተዘጋጅቷል።

የብሉይ ኪዳን ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት

1. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል

2. መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ

3. መጽሐፈ ጦቢት

4. መጽሐፈ ዮዲት

5. መጽሐፈ አስቴር

6. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ፣ ካልእና ሣልስ

9. መጽሐፈ ሲራክ

10. ጸሎተ ምናሴ

11. ተረፈ ኤርሚያስ

12. ሶስና

13. መጽሐፈ ባሮክ

14. መጽሐፈ ጥበብ

15. መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ

16. ተረፈ ዳንኤል

17. መጽሐፈ ኩፋሌ

18. መጽሐፈ ሔኖክ

19. መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን

የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት

⒈ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ

⒉ መጽሐፈ አብጥሊስ

⒊ ግጽው ዘሲኖዶስ

⒋ ሥርዓተ ጽዮን

⒌ መጽሐፈ ዲድስቅልያ

⒍ መጽሐፈ ትእዛዝ

⒎ መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ እና ካልእ

ያውርዱና ብዙ የተደከመበትን መጽሐፍ ቅዱስ በእጅዎ ያስገቡ።

Novità nell'ultima versione 6.1.1

Last updated on Apr 28, 2021

በዚህ ዕትም ከዚህ በፊት ያልተጠናቀቁ መጻሕፍት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው ተካተዋል። እነዚህም
⒈ መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን
⒉ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
⒊ መጽሐፈ አብጥሊስ
⒋ ግጽው ዘሲኖዶስ
⒌ ሥርዓተ ጽዮን
⒍ መጽሐፈ ዲድስቅልያ
⒎ መጽሐፈ ትእዛዝ
⒏ መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ
⒐ መጽሐፈ ኪዳን ካልእ

Traduzione in caricamento...

Informazioni APP aggiuntive

Ultima versione

Richiedi aggiornamento Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ 6.1.1

Caricata da

Ahmed Elraman

È necessario Android

Android 4.1+

Mostra Altro

Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ Screenshot

Commento Loading...
Lingua
Ricerca...
Iscriviti ad APKPure
Sii il primo ad accedere alla versione anticipata, alle notizie e alle guide dei migliori giochi e app Android.
No grazie
Iscrizione
Abbonato con successo!
Ora sei iscritto ad APKPure.
Iscriviti ad APKPure
Sii il primo ad accedere alla versione anticipata, alle notizie e alle guide dei migliori giochi e app Android.
No grazie
Iscrizione
Successo!
Ora sei iscritto alla nostra newsletter.